ጡረታ ስወጣ ያጠራቀምኩትን 401(K) ምን ላድርገው?
እድሜ ፀጋ ነው:: ማንኛውም ሰው አሜሪካን ሀገር መጥቶ ፈጣሪ እድሜ ጤናና ፀጋው አድሎት ለጡረታ መብቃት መባረክ ይመስለኛል:: በሥራ አጋጣሚ የማገኛቸው ሰዎች አሁን ጡረታ መውጣቴ ነው እስካሁን ያጠራቀምኩትን 401(K) ምን ላድርገው በሚል ግራ ሲጋቡ ለመመልከት ችያለው:: ይህ አጭር ፅሑፍ በአንድ ወይንም በተለያዪ መ/ቤቶች ሲሰሩ ያጠራቀምኩትን 401(K) ምን ላድርገው ለሚለው ጥያቄ ያሎትን አማራጮች ከነጥቅምና ጉዳታቸው ለማሳየት የቀርበ ነው:: የተለያዩ አማራጮች እንዳሉ ቢታወቅም ለዛሬ እነዚህን ሦስቱን እንመልከት::
የመጀመሪያው አማራጭ ያጠራቀሙትን ሁሉንም ገንዘብ በአንድ ጊዜ ወጪ ማድረግና ለፈለጉት ዓላማ ማዋል ነው:: የዚህ አማራጭ ጥቅም ገንዘቡን ወዲያውኑ ማግኝት ሲሆን ጉዳቱ እድሜዎ 59 አመት ከ6 ወር በታች ለሆናቸው 10% ቅጣትና ታክስ ሲያሰሩ ክፍያ መኖሩ ነው:::
አማራጭ 2: ጡረታ ሊወጡ ሲሉ ገንዘቡ ይጠራቀምበት የነበረበት መ/ቤት አካውንት ውስጥ እንደነበረ እንዲቀጥል ማድረግ ነዉ:: የዚህ አማራጭ ጥቅሞች (1) የአገልግሎት ክፍያ አነስተኛ መሆኑ:: (2) እድሜያቸው ከ55 እስከ 59 አመት ከ6 ወር በታች ከሆነ “the Rule of 55” በመጠቀም የቅጣት ገንዘብ ማስቀረት መቻሉ:: (3) ገንዘቡ ጠንከር ባለ Creditors Protection የሚጠበቅ መሆኑ:: የዚህ አማራጭ ጉዳቶች (1) የአገልግሎት ክፍያ ከጊዜ በኃላ መጨመሩ:: (2) በፈለጉት ጊዜ ገንዘቡን ማውጣት ያለመቻል:: (3) ብዙ የኢንቨስትመንት አማራጭ ያለመኖር:: (4) የወረቀት ፎርም መሙላት ወይም የስልክ ንግግር ውጣ ውረድ መኖሩ:: (5) ውስን የአማካሪ አገልግሎት::
አማራጭ 3:- የተጠራቀመውን ሁሉንም ገንዘብ ወደ ሌላ የግል የጡረታ አካውንት (IRA) ማዛውር ወይም “Rollover”
ማድረግ:: የዚህ አማራጭ ጥቅሞች (1) አገልግሎት ክፍያ አነስተኛ መሆኑ:: (2) ብዙ የኢንቨስትመንት አማራጭ መኖር::
(3) በፈለጉት ጊዜ ገንዘቡን ማውጣት የሚያስችል ሁኔታ መኖሩ:: (4) አማካሪ በፈለጉት ጊዜና ቦታ ማግኝት መቻሉ:: (5) ከአንድ በላይ 401(K) አካውንት ካሎት በአንድ ቋት እንዲሆን ማድረግ መቻሉ:: የዚህ አማራጭ ጉዳቶች (1) አገልግሎት ክፍያ ከፍተኛ ከሆነ:: (2) እድሜዎ 59 አመትከ6 ወር በታች ከሆነ 10% ቅጣትና ታክስ ሲያሰሩ ክፍያ መኖሩ:: (3) አካውንቱ ሲከፈት የወረቀት ስራ መኖሩ (4) የCreditors Protection የላላ መሆኑ:: (5) እድሜዎ 72 ከሆነ በኃላ ገንዘቡን ከአካውንት የማውጣት ግዴታን ማዘግየት አለመቻሉ:: (6) the Rule of 55” ተግባራዊ ማድረግ አለመቻሉ::
የቱ እንደሚሻል ለማወቅና በዝርዝር ለመረዳት የአመቱን ታክስ የሚሰራሎትን ባለሙያ ያማክሩ:: ገንዘቦንና ጊዜዎን በአግባቡ ይጠቀሙ::
ስለ 401(K) እና ስለጡረታ ሰፋ ያለ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ ፀሐፊውን በ702-934-4075 ማግኝት ይችላሉ::