damonv

ታክስን በጭልፋ!

አዲስ አመት መጥቶ የጃንዋሪ ማብቂያው ላይ የአመቱን ታክስ ለማሰራትና ተመላሽ ገንዘቡን በማሰብ ምን እንደምናረግበት ማሰብ ልማዳችን ነው:: በሌላ አቅጣጭ ደግሞ ቀደም ሲል አሰርተን ለIRS የላክነውን የታክስ ወረቀት በማስተካከል Form 1040-X, Amended Tax Return መላክ ቢያስፈልግ እስከመቼ ነው የምንችለው ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ::

በUncle Sam መመሪያዎች መሰረት አንድ ሰው ታክስ አሰርቶ ለIRS ከላከ በኃላ ተመላሽ ገንዘብ ከነበረው እስከ 3 አመት ባለው ጊዜ ውስጥ ቀደም ሲል ያሰራውን ታክስ ማስተካከያ አድርጎ መላክ ይችላል:: ነገር ግን እዳ ከፋይ የነበረ ከነበረ ግን እዳውን ከከፈለበት ቀን እስከ ሁለት አመት ባለው ጊዜ ውስጥ ቀደም ሲል ያሰራውን ታክስ ማስተካከያ አድርጎ መላክ ይችላል::

ስለ ታክስ ሰፋ ያለ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ የዓመቱን ታክስ የሚሰራሎትን ወይም የዚህ ፅሑፍ አቅራቢን በ702-934-475 ማግኝት ይችላል::

ዳሞ ዘመዴ
ላስቬጋስ ኔቫዳ